Skip to main content
lnews4
ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ በጤና ዘርፍ ሥልጠና ከፍተኛ ልምድ ያካበተው ኮሌጁ ሲዳማ ክልል ከሆነ በኋላ በልዩ ትኩረት እየሠራ ይገኛል። የክልሉ ጤና ቢሮም የቅርብ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ የኮሌጁ የመማር ማስተማር፣የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት፣የተማሪዎች አገልግሎት፣ተያያዥ አስተዳደራዊ ጉዳዮችና ሌሎች የሥራ እንቅስቃሴዎች ሁሉን አቀፍ ስኬት በሚያጎናጽፍ መልኩ እየተመራ ይገኛል። የመማር ማስተማሩን/Academic activities/ ሥራ በተመለከተ ግቢ ውስጥ በንድፈ ሀሳብና ሠርቶ ማሳያ ሥልጠናዎች ተጀምሮ በሆስፕታሎች፣ጤና ጣቢያዎችና ማህበረሰብ ውስጥ በተግባር የሚሠጥ ስሆን ይህ የኮሌጁ ልዩ መገለጫ ሆኖ ለዓመታት የኖረና በቀጣይነትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው። ይህ በልዩ ዲስፕሊን የሚመራው ሥልጠና የኮሌጁን ተመራቂዎች በሄዱበት ሁሉ ስኬታማ ያደረጋቸውና ምስጋና ያስገኘላቸው ትልቅ አሻራ ነዉ። ሲዳማ ክልል ከመሆኑ በፊት በሶስት የሙያ አይነቶች ብቻ ተገድቦ የቆየዉና ከያነዎቹ ሲዳማ ዞንና ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር 28 ኮታ ብቻ ስሰጠዉ የነበረዉ የዲግሪ ፕሮግራም ሲዳማ ክልል ከሆነ በኋላ የፕሮግራሞቹን ቁጥር ሰባት በማድረስ ከሲዳማ ክልል የጤና መዋቅሮች ብቻ በዓመት ከ400 በላይ ተማሪዎችን በማሰልጠን በታሪኩ ልዩ ስኬት ላይ ይገኛል። በኢትዮጵያ ደረጃ የፖስት ቤዚክ ሥልጠና ከሚሰጡ ሶስት ተቋማት ውስጥ አንዱ ነው ኮሌጁ። የዲፕሎማ ሥልጠናም ከዚህ ቀደም ከሚሰጠዉ ብዛትና ጥራት በመስጠት ሁለቱንም ሥልጠናዎችን የሀገሪቱን የሥልጠና ሥርዓተ ትምህርትን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ በማድረግ እየተመራ ይገኛል። በሺዎች የሚቆጠሩ የዲግሪ እና ዲፕሎማ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ስሆን በቀጣይነት የማስተርስ ዲግሪ ሥልጠና ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ረገድም ከፍተኛ በጀት በመመደብ የምርምር ሥራ የሚያከናውን ስሆን በሥራ ዓለም ላሉ የጤና ባለሙዎች ተከታታይ የሙያ ብቃት ሥልጠና በመስጠት ሰርተፊኬት የሚሰጥ በጤና ሚኒስተር ሙሉ ዕውቅና ያለው ኮሌጅ ስሆን ይሄንን በብቃት ለመምራት የCPD ማዕከል በልዩ ሁኔታ ገንብቶ በዘርፉ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጤና ሚኒስተር ከትምህርት ሚኒስተር ጋር በመሆን ሥርዓተ ትምህርት በሚቀርጽበት ወቅት እንደ ዋና መሠረት/Benchmarking / ከሚጠቀምባቸው ጥቂት ተቋት ውስጥ አንዱ ነዉ። በጠንካራ የሰዉ ሀይልና ግብዓት የተሟላዉና ሲዳማ ክልል ከሆነ በኋላ የክልሉን ልዩ ትኩረት አግኝቶ በንቃት እየሠራ ያለው ኮሌጁ የተለያዩ የሪኖቨሽን ሥራዎችን እየሠራ የሚገኝ ስሆን የክልሉን ልዩ ድጋፍ በመጠቀም የውስጥ አደረጃጀቱን በቴክኖሎጂ ለማዘመን በልዩ ትጋት እየሠራ ይገኛል።