admin
Wed, 03/12/2025 - 20:34

ሙሉ የቢሮ አደረጃጀት ያለው ነው፤ ይህም ማለት የራሱ ዳይረክተር፣የሥልጠና ባለሙያዎችን፣የICT ባለሙያችንና የሥልጠና ማኑዋል አዘጋጅ ባለሙያችን/Panel of Experts/ ያሉት፣ ሙሉ ለሙሉ ለብቻዉ ኮሌጁ ውስጥ እንደ ተቋም የተገነባ ማዕከል ያለውና ኢትዮጵያ ውስጥ ይሄንን ማድረግ የቻሉት ጥቂት ተቋማት ናቸው:: ፨ ከፌደራል ጤና ሚኒስተር ፣ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመሆን የትብብር ሥልጠና በማዘጋጀትና በሌሎች ሥርዓቱ በሚፈቅደው መልኩ ሥልጠና በመስጠት ሺዎችን ሰርትፋይ ማድረግ የቻለ የሥልጠና ማዕከል ነው። የኮሌጃችን የCPD ማዕከል ከዚህ ቀደም ከነበረዉ አካሄድ በተለየ መልኩ እየሠራ ያለና እራሱን በቴክኖሎጂ እያደራጀ የክልሉንና የሀገሪቱን የጤና ዘርፍ የሰው ሀይል ልማትን በከፍተኛ ደረጃ እያገዘ የሚገኝ ተቋም ስሆን በየትኛውም ሰዓትና ጊዜ ተገልጋዮችን የከዚህ ቀደም ልምዱንና የአሁኑን ዝግጁነቱን ተጠቅሞ ለማስተናገድ ዝግጁ ነው።