Skip to main content
N4
በዕለቱ የግምገማ መድረኩ ከመጀመሩ አስቀድሞ የኮሌጁን የመማር ማስተማር ሂደቱን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ፤ ከጉብኝቱ በኋላ ዶ/ር ሰላማዊት በሰጡት አስተያየት ኮሌጁ በአሁኑ ወቅት ያለብንን የክህሎት ክፍተትን ሊፈታ የሚችል አቅም እንዳለው ማየታቸውን ተናግረዋል ። ኃላፊዋ አክለውም በጤናው ሴክተር እንደ ክልል '' ለላቀ ውጤትና ለጥራት እንስራ ! '' በሚል ኢኒሼቲቪ ተቀርጾ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ታች ላይ እየታየ ያለውን የስነ-ምግባር፣ የክህሎት፣ የባለቤትነት/ኃላፊነት እንዲሁም ተጠያቂነት ችግሮችን ለመቅረፍ እና የጤናውን ስርዓት በጥራት ለማጠናከር ክፍተቶቻችንን በመፈተሽ እና CPD ላይ የጤና ሥነ-ምግባርና የስራ ባህል ውጤታማነትን በማካተት ይበልጥ ውጤታማ መሆን እንችላለን ሲሉ ተናግረዋል። የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ወ/ሮ ትሁን ፈለቀ በበኩላቸው በጤና ሳይንስ ኮሌጁ በመማር ማስተማር ሂደቱ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ እና ብቁ የሆነ የጤና ባለሙያ ከማፍራት እና አቅምን ከማጎልበት አንጻር በትኩረት እና በጥራት የአሰራር ሥርዓቱንና የሥራ መሠሪያውን ጠብቆ እየሰራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በመጨረሻም የኮሌጁ ዋና ዋና የስራ ዘርፎች ፥ የመማር ማስተማር፣ የምርምር፣ የተማሪዎች አገልግሎትን የያዘ ሰነድም ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። መድረኩን የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ እና ም/ቢሮ ኃላፊና አስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታሪኩ ዱካሞ በጋራ መርተውታል። በእለቱም የጤና ቢሮ ማኔጅመንት፣ የኮሌጁ የአካዳሚክ እና የማኔጅመንት አካላት፣ የስራ ሂደት አስተባባሪዎች ተሳታፊዎች መሆናቸው ታውቋል።